Read more

Mar 13, 2026 .

በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች ለተሠማሩ የቢዝነስ ባለቤቶችና ሴት ሥራ ፈጣሪዎች   ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ።

በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች ለተሠማሩ የቢዝነስ ባለቤቶችና ሴት ሥራ ፈጣሪዎች   ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ።

ሥልጠናው በዲጂታል ማርኬቲንግ እና ኢ ኮሜርስ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ማርኬቲንግ ዙሪያ ያተኮረ ነበር።

ለቀናት በተለያየ የሥልጠና ቡድን ተከፋፍሎ ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወይዘሮ ሔለን ረታ ዲጂታል ማርኬቲንግ ወቅቱን የዋጀ እና ለቢዝነስ ተቋማት ትልቅ አቅም የሚገነባ ሥለመሆኑ ገልጸዋል።

ሰልጣኞቹም በሥልጠናው ያገኙትን እውቀት በአግባቡ ሥራ ላይ ማዋል እንዳለባቸውም ነው ያሣሠቡት።

ምክር ቤቱ ለሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች በሠጠው ትኩረት መሠረት ሴት የቢዝነስ ባለቤቶችና ሥራ ፈጣሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለማሥተዋወቅና ተደራሽ ለማድረግ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ሥልጠና እየሠጠ መሆኑንም አመላክተዋል።

የምክር ቤቱ የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ ብሥራት በለጠ አካዳሚው በበርካታ የቢዝነስ መሥኮች ብቃት ባላቸው አሠልጣኞች የሠልጣኞችን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ሥልጠናዎችን መሥጠት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ሠልጣኞቹ በበኩላቸው በቆይታቸው የተሻለ ግንዛቤ ሥለማግኘታቸውና ከሀገር ውስጥ ባለፈ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት ትግበራ ሂደት በአፍሪካ ገበያ ብሎም በዓለም ገበያ ላይ ምርትና አገልግሎታችውን እንዲያሥተዋውቁ እድል ይፈጥራል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ ዘርፈ- ብዙ ሥልጠናዎችን በመሥጠት የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውሥጥ የመሪነት ሚና እንዲኖረዉ እየሠራ የሚገኝ ሀገራዊ አንጋፋ ምክር ቤት ነው።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia