የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ- ኮሜርስ ዙሪያ ሥልጠና እየሠጠ ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ- ኮሜርስ ዙሪያ ሥልጠና እየሠጠ ነው።
ሥልጠናው የሚሰጠው ለሴት ኢንተርፕረነሮች እና የቢዝነስ ባለቤቶች ነው።
በሥልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሔለን ረታ ምክር ቤቱ ከሚሰራቸው ሥራዎች አንዱ የአቅም ግንባታና ሥልጠና መሆኑን በመግለጽ ለወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት ሠጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
ዲጂታል ማርኬቲንግ እና ኢ ኮሜርስ የገበያ እድልን በማሥፋት ለደንበኞች በቀላሉ ተደራሽ ለመሆን እንዲሁም ለዓለም ገበያ መቅረብ የሚቻልበትን አጋጣሚ የሚፈጥር አሠራር መሆኑን አንስተዋል።
ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ሥልጠናው ሴቶች ቢዝነሶቻቸውን ለማስፋት እንዲሁም ከደንበሥኖቻቸው ጋር ለመገናኘትና አዳዲስ ደንበኞችን ለማፍረት እንደሚረዳም ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች በአካል፣ በኦንላይን እንዲሁም በሌሎች አማራጮች በርካታ ሰልጣኞችን እያሠለጠነ ይገኛል።
ከ1939 ዓ.ም ጀምሮ የግሉን ዘርፍ በመወከል እየሠራ የሚገኘው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ንግድና ኢንቨሥትመንት እንዲስፋፋ፣ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ድልድይ መሆን ህግና አሠራሮች እንዲሥተካከሉ የማድረግ እንዲሁም የአቅም ግንባታና ሥልጠና ዓላማዎችን አንግቦ የሚሠራ ሀገራዊ አንጋፋ ተቋም ነው።

