Read more

Mar 28, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ኤጄንሲዎች ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ::

       

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ኤጄንሲዎች ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ::
ዋና ጸሐፊው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ኤጄንሲዎች ተወካዮች ጋር በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
ዶክተር ቀነኒሳ ምክር ቤቱ በሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት በቀጣይም ከልማት አጋሮች ጋር በትብብር ሊሰራባቸው በሚችሉ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቺፍ ኦፍ ሰፕላይ ማኔጅመንት ሚስተር ጆርጅ ኦቦሮ በበኩላቸው ያለ ግሉ ዘርፍ የነቃ ተሳትፎ ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ እንደማይቻል ጠቅሰው ለዚህም የግሉ ዘርፍ እድገትን ለመደገፍ በትብብር መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በዚህ ረገድም ምክር ቤቱ ተነሳሽነቱን በመውሰድ የግሉ ዘርፍ እድገትን ለመደገፍ ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያደንቁ ገልፀው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎቹ የተባበሩት መንግስታት ኤጄንሲዎች ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃር በጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅሰዋል፡፡

   
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ አመታዊው የቢዝነስ ሴሚናር ሲሆን በተያዘው መርሀ ግብርም የፊታችን ግንቦት ወር አጋማሽ ላር የሚካሄድ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በኩነቱ ላይ የግሉ ዘርፍን ማስተባበር ተሳትፎ እንዲያደርግ ሚስተር ጆርጅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ለቀረበላቸው ጥሪ አመስግነው ምክር ቤቱ ሴሚሩ የተሳካ እንዲሆን አስፈጊውን ተሳትፎና እገዛ እንደሚያደርግም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በተያያዘም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ  ከUNIDO እና UNODC ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ አካላት የግሉን ዘርፍ ልማት ለመደገፍ እና ኢኮኖሚውን ለማቃቃት በሚቻልበት ዙሪያ ነው የተወያዩት፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) በበኩላቸው የምክር ቤቱን ተልዕኮ እና እያከናወናቸው የሚገኙ አበይት ተግባራት እንዲሁም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ኤጄንሲዎችና የልማት አጋሮች ጋር በትብብር ሊሰራባቸው በሚችሉ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ገለፃ አድርገዋል፡፡

የUNIDO ምክትል ተወካይና የፕሮግራም ኦፊሰር አቶ አሰግድ አዳነ በአሁኑ ወቅት ተቋማቸው ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የኢንዱስትሪ ልማትን ለመደገፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አብራርተዋል፡፡
ዘላቂ የኢንዱትሪም ሆነ ጠቅላላ የኢኮኖሚ እድገት የሚረጋገጠው ጠንካራ የግሉል ዘርፍ ሲኖር መሆኑን ያነሱት አቶ አሰግድ ለዚህም ምክር ቤቱ ተነሳሽነቱን በመውሰድ በጋራ ለመስራት ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያደንቁ ገልፀዋል፡፡
ምክር ቤቱ ከUNIDO ጋር በጋራ ለመስራት ሰፊ እድሎች እንዳሉ አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል የUNIDO የአምስት አመት Country Partnership Framework ሰነድ ዝግጅት በቅርቡ እንደሚጀመር ገልፀው ግብአት ለማግኘት ከም/ቤቱ ጋር ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
የUNODC ተወካይ ሚስተር ቤንጃሚን በበኩላቸው ተቋማቸው በአሁኑ ወቅት የቢዝነስ ስነ-ምግባር (Business integrity) ፖሊሲ የማዘጋጀትና የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ የሰልጠና መረሀ-ግብሮች እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ከEthical business ጋር በተገናኘ በጋራ ለመስራት በድርጅታቸው በኩል ከምክር ቤቱ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውም አንስተዋል ፡፡
ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር የተደረገው ፍሬያማ ውይይትም በጋራ እና በትብብር ለመስራት በር ከፋች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia