Read more

Mar 28, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከ Breakthrough ድርጅት የዴሬክተሮች ቦርድ እና የጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ ሊተገበሩ በሚችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

       

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከ Breakthrough ድርጅት የዴሬክተሮች ቦርድ እና የጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ ሊተገበሩ በሚችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡
በአዲስ አበባ በቅርቡ ለማካሄድ በታቀደውና በቀጥታ ሽያጭ ዙሪያ የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊነት፤ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታና የአገራት ምርጥ ተሞክሮዎች አንዲሁም አሰራሩ ከዓለም አቀፍና አህጉራዊ የንግድ ድርጅቶች ጋር የሚኖረው መስተጋብር የሚዳሰስበት፤ በተጨማሪም  የቀጥታ ሽያጭ  በስራ ዕድል ፈጠራ፤ በሴቶችና ወጣቶች አቅም ግንባታ ዙሪያ ባለው ፋይዳ ላይ ጥናት ቀርቦ ምክክር የሚካሄድበት መድረክ ውጤታማነት ዙሪያ ሁለቱ አካላት በጋራ በሚያከናውኗቸው ዝርዝር ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

   
የBreakthrough Trading S.C የዴሬክተሮች ቦርድ እና የጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች ድርጅቱ በሚሰራቸው ስራዎች ዙሪያ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን፤ ተቋማቸው የሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ካስቀመጣቸው ስትራቴጂካዊ ግቦች አንጻር አብረው የሚሄዱ በመሆኑ፤ በጋራ መስራታችን አገራችን ከምትፈልገው ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚያዊ እድገት አንጻር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
የመንግስት ባለድርሻ አካላት፤ የግሉ ዘርፍ እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ እና አህጉራዊ ድርጅቶች እንደሚሳተፉበት የሚጠበቀው ይህ መድረክ በቀጥታ ሽያጭ ዙሪያ ያሉ የህግ አሰራሮች የሚፈተሹበት እንዲሁም የሚኖረው አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በዝርዝር የሚቀርብበት እና በጉዳዩ ዙሪያ ከመንግስት ጋር ለሚደረግ ውይይት የሚቀርቡ ሃሳቦች የሚለዩበት እንደሆነም በጋራ የውይይት መድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

 
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በተደረገው በዚህ ውይይት ላይም  የ Breakthrough Trading S.C  ሊቀመንበር አቶ ኢሳያስ ቡልቶን ጨምሮ የድርጅቱ የዴሬክተሮች ቦርድ እና የጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች  የተገኙ ሲሆን ፤ በምክር ቤቱ በኩልም ዋና ፀሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በተጨማሪ ሌሎች የምክር ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia