የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በንግድ ማሳለጥ (Trade facilitation) ዘርፍ የሚሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በንግድ ማሳለጥ (Trade facilitation) ዘርፍ የሚሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች
ምክር ቤቱ ለንግዱ ማህበረሰብ የተሳለጠ የቢዝነስ ከባቢ ለመፍጠር፣ ለኢትዮጵያ ምርትና አገልግሎቶች ምቹ ገበያ እንዲያገኙ የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ስለሆነም፡
የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት ሚና (leading role) እንዲጫዎት እንዲሁም ምቹ የቢዝነስ ከባቢ እንዲኖር ለማስቻል የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ በተለይም ለተሳለጠ ንግድ መኖር የሚሰጣቸው አገልግሎቶችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
- የአምራች አገር ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (Certificate of Origin)
ይህ የምስክር ወረቀት በኢትዮጵያ የተመረቱ ምርቶች ኢትዮጵያዊ ስለመሆናቸው የሚሰጥ ማረጋገጫ ሲሆን እንደ ምርቱ ፓስፖርት የሚቆጠር ምስክር ወረቀት ነው፡፡ ይህም ተመሳስለው ከውጭ ገብተው ተመልሰው ወደ ውጭ እንዳይወጡ በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ምርቶች የተሻለ ገበያ እንዲያገኙና መነሻቸው እንዲታወቅ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡
ይህ ሰነድ በምርት ተቀባይ ሀገራት በኩል በሚገዙበት ወቅት ኢትዮጵያዊ ምርት ስለመግዛታቸው የሚያረጋግጡበት ሰርቲፊኬት ነው፡፡ የአምራች ሀገር ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ፕሪፈረንሺያል/Preferential Certificate of Origin እና ኦርዲናሪ (Non Preferential Certificate of Origin) ተብሎ ይከፈላል፡፡
ፕሪፈረንሺያል (Preferential Certificate of Origin) የአምራች አገር ማረጋገጫ በዋናነት በጉምረክ ኮሚሽን በኩል የሚሰጥና ከታክስ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ሲሆን ኦርዲናሪ (Non Preferential Certificate of Origin) ደግሞ የምርቱን መነሻ ብቻ የሚያመላክት ከታክስ ጉዳዮች ጋር ያልተገናኘ ምስክር ወረቀት ነው፡፡

በሌላ በኩል ከውጭ የገቡ እና በተለያዬ ምክንያት ተመልሰው ወደ ውጭ የሚወጡ ምርቶች ከሆኑ ደግሞ በምክር ቤቱ በኩል ተመልሰው የሚወጡ ስለመሆናቸው re-export certificate ይሰጣቸዋል ማለት ነው፡፡
የግብርና ምርቶች፣ የቅባት እህሎች፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ሌሎች ምርቶች በዚህ የምስክር ወረቀት ወደ ውጭ ገበያ የሚላኩ ሀገራዊ ምርቶች ናቸው፡፡
ምክር ቤቱ በአሁኑ ወቅት በኦንላይን እየሰጣቸው ከሚገኙ አገልግሎቶች ቀዳሚው ነው፡፡

2. የኮሜሳ ምስክር ወቀረት (COMESA Certificate)
ይህ ሰነድ የሚሰጠው የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ ተለያዩ የምስራቅና የደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ ወይም ኮሜሳ አባል ሀገራት ሲላኩ ነው፡፡

ይህ ሰርቲፊኬት Preferential Certificate ሲሆን ከታክስ ጋር የተያያዘም ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር ያላት የ10 በመቶ የግብር ቅናሽ በመሆኑ እንደሌሎቹ ሁሉ ይህንን ሰርቲፊኬት ያገኘ ነጋዴ የ10 በመቶ የታክስ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡
- የኤክስፖርት ዋጋ መግለጫ (Invoice and Packing List) እንዲሁም የነጻ ሽያጭ እና የጤና ሰርቲፊኬት (Free Sales and Health Certificate) ሰነዶች
እነዚህ ሰነዶች አስፈላጊ የወጭ ንግድ መረጃዎች ሲሆኑ በምክር ቤቱ በኩል ተረጋግጠው የሚሰጡ ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ የFree Sales and Health Certificate ሰነዶች በምግብና መድሀኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በኩል መረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ምርቶቹ ለምግብነት ስለመዋላቸው ማረጋገጫ ከሰጠ በኋላ በምክር ቤቱ በኩል ማረጋገጫ ይሰጣቸዋል፡፡ የዋጋ ማረጋገጫ እና የፓኪንግ ዝርዝር አስፈላጊ ሰነዶች ሲሆኑ ተቀባይ ሀገራት የሚፈልጓቸው መረጃዎች ናቸው፡፡
- የድጋፍ ደብዳቤዎች
እነዚህ ሰነዶች ነጋዴዎ ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሄድ ትስስር እንዲፈጥ ለምርትና አገልግሎታቸው ገበያ እንዲያገኙ የሚጻፉ ሲሆን ነጋዴ ስለመሆናቸው እና የሚሰሩት ስራ ምን እንደሆነ የሚገልጽ አስፈላጊ ዶክመንቶች ናቸው፡፡ ይህም ምክር ቤቱ ገበያ እና የቢዝነስ ትስስር እንዲፈጥሩ
- ለተለያዩ ሰነዶች ማረጋገጫ መስጠት
እነዚህ ሰነዶች በተለያየ መልኩ ሊሰጡ የሚችሉ ሆነው ከውጭ ሀገራት ማረጋገጫዎች ሲጠየቁ ወይም ሌሎች ማረጋገጫ የሚያስፈልጋቸው መረጃዎች ከነገዴዎች ወደ ምክር ቤቱ ሲመጡ እና ከምክር ቤቱ ዓላማዎች እና ተግባራት ጋር ተያያዥነት ካላቸው ታይተው ማረጋገጫ የሚሰጥባቸው ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለንግዱ ማህበረሰብ የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመንና ቀልጣፋ በማድረግ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር የተሻለ የንግድ ስርዓት እንዲፈጠር፣ ለቢዝነስ ማህረሰቡ የተሻለ የገበያ አማራጭ እንዲኖር እና የኢትዮጵያ ምርቶች ተፈላጊ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
ምክር ቤቱ የአምራች አገር ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (Certificate of Origin) በኦንላይን አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን የኮሜሳ ምስክር ወቀረት (COMESA Certificate) በተመሳሳይ የኦንላይን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ነው፡፡ ስለሆነም የንግዱ ማህበረሰብም ከምክር ቤቱ ጋር ተቀራርቦ እንዲሰራ ያስገነዝባል፡፡

