Read more

Feb 26, 2025 .

10ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የፊታችን ሐምሌ 11/2016 ዓም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

10ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የፊታችን ሐምሌ 11/2016 ዓም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት መልአኩ እዘዘው (ኢንጂነር) እና ዋና ጸሐፊው አቶ ውቤ መንግስቱ በሰጡት መግለጫ ምክር ቤቱ ከ2012 በኃላ በተለያዩ ምክንያቶች ጉባዔውን ሳይካሄድ መቆየቱ ገልፀዋል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው ጠቅላላ ጉባኤው የፊታችን ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም እንዲካሄድ ውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡ ለዚህም የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የገለጹት የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት መልአኩ እዘዘው (ኢንጂነር) አዳዲሶቹ ክልሎችም የሚሳተፉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

በ10ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት፣ ምክትል ፕሬዚደንት እና የቦርድ አባላት ይመረጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የጠቅላላ ጉባኤው መዘግየት በቦርድ አመራሩም ሆነ በስራ ላይ ጫና ሲያሳድር እንደነበር ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላላ ጉባኤው 177 መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን የሚመረጠው ፕሬዚደንትም ምክር ቤቱን የሚመራው 23ኛው ፕሬዚደንት ይሆናል ማለት ነው፡፡

ምክር ቤቱ የቢዝነስ ሊደርሺፕ አካዳሚ በማቋቋም፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት በመስጠት፣ ለአባላት በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ማስተዋወቅና በሌሎች አግባቦች ከመንግስትም፣ ከግሉ ዘርፍ ተዋናዮች እና ከልማት አጋሮች ጋር እየሰራ መሆኑን የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ አቶ ውቤ መንስቱ ገልጸዋል፡፡

ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው አንጋፋው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግሉ ዘርፍ ድምጽ በመሆን ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ የአቅም ግንባታ፣ በአድቮኬሲ እና ምርምር እንዲሁም በሌሎች መስኮች በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia