የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር ጋር ተወያየ::



የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር ጋር በአባላት የአቅም ግንባታ ዙሪያ አብሮ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያየ።
በኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የተመራ የም/ቤቱ ማኔጅመንት፤ አባል ከሆኑት የዘርፍ ማህበራት አንዱ ከሆነው የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ዋና ስራ አስኪያጅ ጋር በነበረው ውይይት በማህበሩ አባላት የአቅም ግንባታ ዙርያ አብሮ ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል።




የኢ/ን/ዘ/ማ/ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከወትሮው በተሻለ ሁኔታ ለመስራት እራሱን በአዲስ መልክ አደራጅቶና መዋቅራዊ ለውጥ አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አሉላ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው አሁን ላይ የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የግሉ ዘርፍ ትክክለኛ ድምፅ ሊሆን ወደ ሚያስችለው ቁመና እየመጣ መሆኑን ጠቅሰው ም/ቤቱ የጀመረውን የሪፎርም ስራ አጠናክሮ ከቀጠለ ማህበራቸው የሚጠበቅበትን የአባልነት ግዴታውን እየተወጣ የም/ቤቱን አቅም በአግባቡ ለመጠቀም ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል።




