Feb 26, 2025 .
አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢርን የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አድርጎ መረጠ።
ጠቅላላ ጉባኤው ዶክተር አይናለም አባይነሕ ን ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ዘጠኝ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን መርጧል።
ጠቅላላ ጉባኤው ከቀረቡለት 3 የፕሬዚደንት፣ 4 የምክትል ፕሬዚደንት እና 16 የቦርድ አባላት እጩዎች መካከል ነው የቦርድ አመራሮቹን የመረጠው።
ጉባኤው ላለፉት 6 ዓመታት የመሩትን የቦርድ አባላት ሲያሠናብት አዳዲሶቹን ክልሎች የምክር ቤት አባልነት ጥያቄ አጽድቋል።
በዚህም መሠረት የደቡብ ክልል፣ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲሁም የሲዳማ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምከር ቤቶችን ነው በአባልነት ያካተተው።

