Read more

May 27, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር ጋር ተወያየ::

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር   ጋር  በአባላት የአቅም ግንባታ ዙሪያ  አብሮ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያየ።

በኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የተመራ የም/ቤቱ ማኔጅመንት፤ አባል ከሆኑት የዘርፍ ማህበራት አንዱ ከሆነው የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር  የዳይሬክተሮች ቦርድ  አባላትና  ዋና ስራ አስኪያጅ ጋር  በነበረው  ውይይት በማህበሩ አባላት  የአቅም ግንባታ ዙርያ አብሮ ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል።

የኢ/ን/ዘ/ማ/ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ  በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከወትሮው በተሻለ ሁኔታ ለመስራት እራሱን በአዲስ መልክ አደራጅቶና መዋቅራዊ ለውጥ አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አሉላ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው አሁን ላይ የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የግሉ ዘርፍ ትክክለኛ ድምፅ ሊሆን   ወደ ሚያስችለው ቁመና እየመጣ መሆኑን ጠቅሰው ም/ቤቱ የጀመረውን የሪፎርም ስራ አጠናክሮ ከቀጠለ ማህበራቸው የሚጠበቅበትን የአባልነት ግዴታውን እየተወጣ የም/ቤቱን አቅም በአግባቡ ለመጠቀም ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart (0 items)

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia