የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራትንምክር ቤት SNV ከተሠኘ ተቋም ጋር በመተባበር በዲጂታል ማርኬቲንግ እና ኢ-ኮሜርስ ዙሪያ ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ሥልጠና እየሠጠ ነው።


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራትንምክር ቤት SNV ከተሠኘ ተቋም ጋር በመተባበር በዲጂታል ማርኬቲንግ እና ኢ-ኮሜርስ ዙሪያ ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ሥልጠና እየሠጠ ነው።
ሥልጠናው በዲጂታል ቴክኖሎጅ አጠቃቀም እንዲሁም በኢ ኮሜርስ እና ተያያዥ የማኀበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ ምርትና አገልግሎትን ማስተዋወቅና የገበያ ትስስር መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
በሥልጠናው ማሥጀመሪያ ላይ የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሔለን ረታ ምክር ቤቱ የግሉን ዘርፍ ወካይ ሀገራዊ ተቋም በመሆኑ በተለያዩ መሥኮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሥጠት አንዱ ተግባር መሆኑን በመጠቆም ከSNV ጋር በመተባበር የሚሠጠው ሥልጠናም መካከለኛና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን (SMEs) ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ ተቋማት ዲጂታል ቴክኖሎጅን በአግባቡ መጠቀም እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።


የዲጂታል ማርኬቲንግ እና የኢ ኮሜርስ አሠራሮች ተቋማት ምርቶቻቸውን ካሉበት ሆነው ከሀገር ውሥጥ ባለፈ ለመላው ዓለም ለማሥተዋወቅና ገበያቸውን ለማስፋት የሚያግዝ በመሆኑ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በሥልጠናውም በቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ በባልትና፣ በአልባሣት እንዲሁም በወጭ እና ገቢ ንግድና በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሣታፊ ናቸው።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በዋናነት ንግድና ኢንቨሥትመንት እንዲሥፋፋ፣ የምርምርና አድቮኬሲ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሥራዎችን የሚሠራ “የግሉ ዘርፍ ድምጽ” የሆነ ሀገራዊ ተቋም ነው።

