Mar 12, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ለሴት የቢዝነስ ባለቤቶች በአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጣና ፕሮቶኮል (AfCFTA) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ::



የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ ሴት ኢንተርፕረነሮች እና የቢዝነስ ባለቤቶች በአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጣና ፕሮቶኮል (AfCFTA) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው::
የግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ ተገኝተው ስልጠናውን ያስጀመሩት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሔለን ረታ ምክር ቤቱ ለኢንተርፕረነሮችና የቢዝነስ ባለቤቶችን አቅም ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እየሰራ መሆኑን አስታውሰው፣ ሴቶች ከዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ-ኮመርስ በተጨማሪ የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጣና ያላቸውን እውቀትና ግንዛቤ በማሳደግ ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት እንደሚገባ ገልፀው ፣ ስልጠናውን በንቃት መከታተል ከሰልጣኞች የሚጠበቅ መሆኑን አሳስበዋል ፡፡

ስልጠናው የአፍሪካ አህጉር የንግድ ቀጣና ምንነት፣ ስምምነት፣ ዓላማ፣ እንዲሁም ለሴቶችና ወጣቶች ያሉ የገበያ እድሎች(protocol on Women and Youth in trade) ላይ ያተኮረ ነው፡፡

