Read more

Nov 10, 2025 .

ህዳር 06 /03/2018 በሰመራ ሎግያ ከተማ መስተዳደር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የከተሞች ፎረምን ይመለከታል::

በመላው አፋር ለምትገኙ የንግዱ ማኅበረሰብ በሙሉ

ጉዳዪ – ሀዳር 06 /03/2018 በሰመራ ሎግያ ከተማ መስተዳደር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የከተሞች ፎረምን ይመለከታል

ለ10ኛ ጊዜ የሚካሄደው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ዝግጅት ለክልሉ የንግድ እንቅስቃሴ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ሲሆን በሀገራችንም ሆነ በክልላችን ፤ እዚህም እዚያም እየተከሰቱ በነበሩና ባሉ የሰላም እጦቶች ምክንያት እየተቀዛቀዘ የነበረውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማንሰራራት ይህን መሰል ዝግጅት ከፍተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ የንግዱ ህብረተሰብም የራሱን ስራ እንደወትሮው ከመከወን ባሻገር ይህን ፕሮግራም እንደራሱ በማየት ከወትሮው እንቅስቃሴው በተለየ መልኩ ከክልላችን መንግስት ጎን በመሆን ሰላምን ከማረጋገጥ ጀምሮ የበኩሉን አስተዋፆ ሊያበረክት ይገባል።

የንግዱ ህብረተሰብ በአንክሮ ሊመለከታቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል ፈር የሳቱና የእንግዶቻችንንም ሆነ የህብረተሰቡን ሰላማዊ ኑሮ ለችግር የሚዳርጉ ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊቶች – (የታማኝነት መጓደል)፣ ማጭበርበር፣) የተጋነነ ትርፍ )፡ ቅንነትና መልካም ስነ ምግባር )፣ ጥራቱን የጠበቀ ምርት አለማቅረብና የማይተነበይ ትርፍ መጠበቅ፣ እንዲሁም የኮሊደር መሰረተ ልማት ያረፈባቸውን አካባቢ ለብክለትና ለጉዳት የሚዳርጉ መሰል ድርጊቶቶችን በነቂስ በመከታተል እንግዶቻችን በአፋር ምድር ከመንገድ ጉዞ ጀምሮ በሁሉም አገልግሎት ደስተኛ ሁነው በሰላም እንዲመለሱ አደራ አማና በማለት የአፋር ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ሃጂ መሐመድ ሽሒም ሀሰን ጥሪ አቅርበዋል።

(የአፋር ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart (0 items)

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia