Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 20, 2026 .

ለቅመማ ቅመም ዘርፍ ማኀበር አባላት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ዙሪያ  በቅመማ ቅመም ዘርፍ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላትና ለዘርፉ ማኅበር አባላት ሥልጠና ተሰጠ::

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለቅመማ ቅመም ዘርፍ ማኀበር አባላት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ዙሪያ  በቅመማ ቅመም ዘርፍ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላትና ለዘርፉ ማኅበር አባላት በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና  ስምምነት (AfCFTA) ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ነው።

ከGIZ-AU ጋር በመተባበር እየተሰጠ ያለው ይህ ስልጠና ዋና ዓላማ በቅመማ ቅመም ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾችና ላኪዎች የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት የሚፈጥራቸውን የገበያ ዕድሎች በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ፣ አስፈላጊውን የንግድ ዕውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ እንዲሁም በአህጉራዊው ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀርቡ ማገዝ ነው።

የምክር ቤቱ ም/ዋና ጸሐፊ ወይዘሮ ሔለን ረታ፣ ምክር ቤቱ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰማሩ አምራቾችና ላኪዎች ስለ አፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና የሚፈጥራቸውን የገበያ ዕድሎች በመጠቀም ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያሳድጉ እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰፊሳ አባቡ በበኩላቸው የቅመማ ቅመም ዘርፍ ከፍተኛ የልማትና የገበያ ዕድል ያለው ዘርፍ መሆኑን ጠቁመው፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ለዘርፉ ተጨማሪ የገበያ ዕድሎችን ሊፈጥር እንደሚችል አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ለቅመማ ቅመም ምርት ምቹ የሆነ መሬትና የአየር ንብረት ያላት መሆኗ ለዘርፉ ልማትና ለወጪ ንግድ መስፋፋት ሰፊ ዕድል ይፈጥራል። ይህንንም አቅም በአግባቡ በመጠቀም የምርት ጥራትን ማሻሻል፣ የወጪ ንግድ አቅምን ማሳደግና ወደ አዳዲስ ገበያዎች መግባት ለዘርፉ ዕድገት ወሳኝ ናቸው።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia