Feb 26, 2025 .
መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለጳጉሜን 2 የሪፎርም ቀን አደረሳችሁ።
ጳጉሜን 2 የሪፎርም ቀን
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ምህበራት ምክር ቤት የንግድ ማህበረሰቡ የጋራ ፍላጎቶችን በሚገባ መንጸባረቅና መሟላታቸውን እንዲሁም ንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የሚሰራ ተቋም ነው፡፡
ከዚህም ባሻገር ፤ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ምክክር በማድረግ፣ የአቅም ግንባታና የቅንጅት ሥራዎችን በማስፋፋት ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ እንዲፈጠርና የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት ሚናውን እንዲጫወት ማድረግ ተልዕኮ ያለው ነው፡፡
ዓላማዎቹን በሚፈለገው ብቃት ልክ እና ደረጃ ማስፈጸም እንዲቻለውም የነበሩ ጠንካራ ስራዎችን የበለጠ በማሳደግ እንዲሁም ዘመኑ ከሚፈልገው አጠቃላይ የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ አንጻር የለውጥ እና ሪፎርም ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማከናወን፤ የንግዱ ማኅበረሰብ በሚገባው ደረጃ እና ቁመና ልክ እንዲሆን ለማስቻል በሙሉ ቁርጠኝነት እየሰራን ነው::
እነዚህን እና ሌሎች የምክር ቤታችንን ተልዕኮዎቻች ለማሳካት በምናደርገው ሰፊ ጥረትም ከጎናችን በመሆን እየደገፋቹን ላላቹ ሁሉ በዚህ አጋጣሚ ምስጋናየን አቀርባለው ፡፡
መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለጳጉሜን 2 የሪፎርም ቀን አደረሳችሁ።
ስብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

