Feb 26, 2025 .
መንግስት የግሉን ዘርፍ እያነቃቃ መገኘቱ ምርታማነትንና ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ልማታችንን ከግብ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያችንን ለማጠናከር
ከምንጊዜዉም በበለጠ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የግሉን ዘርፍ እያነቃቃ መገኘቱ ምርታማነትንና ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ልማታችንን ከግብ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያችንን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ገለፁ።
አክለዉም፤ ይህም ለአፍርካ የነፃ ንግድ ቀጠና እና ለለሎችም የዓለም ገበያዎች ጥሩ ዝግጅት እንዲኖረን ያደርጋል ብለዋል ::
ምክር ቤታችንም የኢትዮጵያ ታምርት እና የኢትዮጵያን ይግዙ ንቅናቄን በአገር ዉስጥና በዉጭ ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት በሰፊው እየሰራ ነው ሲሉም አጠቃለዋል።

