Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Apr 11, 2026 .

መዓድ ማጋራት ማህበራዊ ኃላፊነታችን ነው:- ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

መዓድ ማጋራት ማህበራዊ ኃላፊነታችን ነው!

በተፈጥሮ ወይም በሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት የሚፈጠሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅነስ፣ በተለይም አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ኑሯቸውን ማሸነፍ ሲከብዳቸው እና በተለያዩ መንገዶች ለሚከሰቱ ችግሮች ዕልባት ለመስጠት ከምናከናውናቸው ማህበራዊ እሴቶቻችን አንዱ ሲሆን፣ በፈጣሪና በሰዎች ዘንድ ከሚከበሩ የተቀደሱ ተግባራት መካከልም አንዱ ነው።

በተለይም ግለሰቦች፣ ባለሀብቶችና የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች በራሳቸው ተነሳሽነት በሰፊው የሚያከናውኑት የበጎ አድራጎት ሥራ ምስጋና ሊቸረው ይገባል።

መንግስትም በበኩሉ ባለሀብቶች የማህበራዊ ግዴታቸውን (Corporate Social Responsibility) እንዲወጡ በማበረታታት፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በአቅመ ዳካማ ወገኖቻችን መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ “ገበታ ለሀገር” እና ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ውስጥ በማሳተፍ ውጤታማ ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው።

ሌላው እንደ  ተሞክሮ መወሰድ የሚችል በኦሮሚያ ክልልም ከተረጂነት በዘላቂነት ለመላቀቅ የሚያስችሉ እንደ “ቡሳ ጎነፋ” ያሉ ተቋማት በተደራጀ መልኩ ተቋቁመው ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጡ ናቸው።

ሆኖም አንዳንድ ጊዜ የበጎ አድራጎት ሥራን ግለሰቦች የራሳቸው ዝና ማካበቻ ሲያደርጉና የዜጎችን ሰብአዊ መብት ባላካባረ እና የሀገር ገፅታን በሚያበላሽ መልኩ  ተረጅዎችን እና የተርጅ ቤተሰቦችን  የምያሸማቅቅ ፎቶ እና ቪድዮ በማጋራት ለሚዲያ ፍጆታ የሚደረግ ከባህልና ከሕግ ያፈነገጠ ተግባር ፈር መያዝ አለበት።

ማዕድ ማጋራት ከልብ የሚመነጭ የአብሮነት እሴት ነዉና ሁሉም ካለው ለሌለው ያጋራ!

መልካም በዓል!

 

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት  ፕሬዚደንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia