Sep 07, 2025 .
በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል በሚደረጉ ምክክሮች (Public – Private Dialogue) ስምምነት ላይ በተደረሠባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ!

በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል በሚደረጉ ምክክሮች (Public – Private Dialogue) ስምምነት ላይ በተደረሠባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ!
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት፣ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና ከግብርና ሚኒስቴር ከተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ነው ውይይት የተካሄደው።
በግብርና ምርቶች እሴት ስንሰለት እንዲሁም የገበያ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ምክክሮች ሲደረጉ ቆይተዋል።
በአሁኑ ወቅትም በግብርና ምርቶች የእሴት ሠንሠለት ዙሪያ የሚታዩ ተግዳሮቶች እና
መፍትሄዎቻችው ዙሪያ የተገኙ ውጤቶችና በቀጣይም የግብርና ምርቶች ከአመራረት፣ ከመረጃ እና ግብዓት እሥከ ዓለም አቀፍ ገበያ ድረሥ ያሉ የእሴት ሠንሠለት ስራዎች ( Value chain) በውይይቱ ተዳሠዋል።
የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ የተጀመረው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርድ ማኀበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በ2002 ዓ.ም ነው።
ባለፉት ዓመታትም በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክሮች ተደርገው በተገኘው ግብዓት መሠረት የተለያዩ የህግና አሠራር ማሻሻያዎች መደረጋቸው ይታወቃል።


