በምክር ቤቱ የ2019 በጀት ዘመን ረቂቅ ዓመታዊ እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረግን በኋላ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን በማከል አፅድቀናል:- ሰብስብ አባፊራ

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታወን ONE THIBAULT HOTEL ፤ በምክር ቤቱ የ2019 በጀት ዘመን ረቂቅ ዓመታዊ እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረግን በኋላ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን በማከል አፅድቀናል።
በተካሄደው የ2019 በጀት ዘመን ረቂቅ ዓመታዊ እቅድ ውይይት፤ ከፅ/ ቤቱ የቀረበልንን የስራ እንዲሁም የበጀት እቅዶች በዝርዝር የተመለከትን ሲሆን፤ ምክር ቤቱ የሚጠበቅበትን የግል ዘርፍ ተልዕኮ ከማሳካት አንፃር የቀረበው ዕቅድ ሙያዊ መሆኑን በማንሳት በተጨማሪም ሊከናወኑ የሚገባቸው ወቅታዊ ቁልፍ ተግባራትን በማከል በሙሉ ድምፅ አፅድቀናል።
የቀረበው ዕቅድ የምክር ቤቱን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ፣ ወቅታዊ የግሉ ዘርፍ ነባራዊ ሁኔታን፣ በአገራችን ያለውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ፣ የግሉ ዘርፍ ፍላጎቶችን፣ የምክር ቤቱን ቀጣይ የለውጥ ጉዞን ብሎም ያለውን አቅም መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ለዕቅዱ መሳካት የምክር ቤቱ የዴሬክተሮች ቦርድ፣ የፅ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ለአፈፃፀሙ ተግተው እንዲንቀሳቀሱ እንዲሁም ተባባሪና የባለድርሻ አካላት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት
At the One Thibault Hotel in Cape Town, South Africa, the Board of Directors of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations held extensive discussions on the Chamber’s draft annual plan for the 2019 Ethiopian fiscal year.
Following these deliberations, we approved the plan with a number of amendments.
During today’s discussion on the draft annual plan for the 2019 fiscal year, we thoroughly reviewed the work programme and budget proposals submitted by the Secretariat. We noted that the plan is professionally prepared and well aligned with the Chamber’s mandate of advancing the interests of the private sector.
We also incorporated additional priority activities that reflect current realities and emerging needs before unanimously approving the plan.
The proposed plan has been developed on the basis of the Chamber’s five-year strategic plan, the prevailing conditions of the private sector, the ongoing economic transformation taking place in our country, the needs and aspirations of the business community, the Chamber’s continuing reform journey, and its existing institutional capacity.
To ensure the successful implementation of the plan, I would like to take this opportunity to call upon the Chamber’s Board of Directors, the management and staff of the Secretariat, to work with dedication and commitment towards its effective execution. I also urge our partners and stakeholders to continue strengthening their support and cooperation as we strive to achieve our shared objectives.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

