በብሪክስ ላይ ያተኮረ ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ተግባራዊ ልማት” የተሰኘ የባለሙያዎች ውይይት በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡


በብሪክስ ላይ ያተኮረ ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ተግባራዊ ልማት” የተሰኘ የባለሙያዎች ውይይት በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡
“ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ የልማት ተግባር” በሚል መሪ ርዕስ የBRICS የባለሙያዎች ውይይት በአዲስ አበባ ሲካሄድ ውይይቱ የ18ኛው የBRICS ጉባኤ ውጤቶችን ወደ ተጨባጭ የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት፣ የቴክኖሎጂ፣ የንግድ እና የትብብር ዕድሎች መቀየር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጓል።
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) ባዘጋጀው በዚህ ውይይት ከመንግሥት፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከምርምር ተቋማት እና ከሌሎች ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (ECCSA) የBRICS ኒው ዴልሂ 2026 ዲክሌሬሽን ወደ ተጨባጭ የንግድ ውጤቶች ለመቀየር የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን አቅርቧል።
የምክር ቤቱ የምርምርና የአድቮኬሲ ዳይሬክተር አቶ ታከለ አየለ በዲፕሎማሲያዊ ቃል ኪዳኖችና በግሉ ዘርፍ ዕድገት መካከል ያለውን ክፍተት ለማጥበብ የሚያስችሉ ተግባራዊ ዘዴዎችን ያቀረቡ ሲሆን የገበያ ተደራሽነት፣ የንግድ ትብብር፣ የፈጠራ እና የእሴት ሰንሰለት ላይ በማተኮር እንደ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣ ሥጋ፣ እንስሳት እና አግሮ-ፕሮሰስድ ምርቶች የወጪ ንግድ ዘርፎች ላይ ያሉ ዕድሎችን ዳሰዋል።

ከመንግሥት-ለ-መንግሥት ግንኙነት በተጨማሪ የምክር ቤት-ለ-ምክር ቤት ትብብር፣ የቢዝነስ-ለ-ቢዝነስ (B2B) አጋርነት እና ያልተቋረጠ የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ማጠናከር እንደሚያስፈልግም አቶ ታከለ አብራርተዋል፡፡
ውይይቱም የBRICS ትብብርን ወደ ኢንቨስትመንት፣ ንግድ መስፋፋትና አጋርነት፣ የቴክኖሎጂ ትብብር እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራዊ አማራጮችን ለመቃኘት አስፈላጊ መሆኑም ተገልጿል፡፡
……………………………
Expert-Level Dialogue on BRICS “From Diplomatic Engagement to Development Action” Held in Addis Ababa.
An expert-level dialogue on BRICS, themed “From Diplomatic Engagement to Development Action,” was held in Addis Ababa, focusing on how to translate the outcomes of the 18th BRICS Summit into tangible opportunities for Ethiopia in investment, technology, trade, and sectoral cooperation.
The dialogue was organized by the Institute of Foreign Affairs (IFA) of the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia and brought together stakeholders from government, the private sector, research institutions, and other relevant organizations.
The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) outlined strategic pathways for transforming the BRICS New Delhi 2026 Declaration into concrete commercial outcomes for Ethiopia.
Representing ECCSA, Mr. Takele Ayele, Research and Advocacy Director, presented actionable mechanisms to bridge the gap between diplomatic commitments and private-sector growth. He emphasized the importance of market access, trade cooperation, value creation, and value-chain integration across key Ethiopian export sectors, including coffee, oilseeds, pulses, meat, livestock, and agro-processed products.
Mr. Takele further highlighted the need to move beyond traditional government-to-government relations toward stronger chamber-to-chamber cooperation, business-to-business (B2B) partnerships, and seamless cross-border trade.
The dialogue provided an important platform for stakeholders to explore practical ways of turning diplomatic engagement into investment, trade, business partnerships, and sustainable development outcomes for Ethiopia.

