Nov 12, 2026 .
በተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራውና የምክር ቤቱን የቦርድ አባላት ያካተተው ልዑክ፣ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በኤግዚቢሽኑ ተሳትፏል።

በሮም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ፣ በቦሎኛ በተካሄደው EIMA International 2026 ዓለም አቀፍ የግብርና ማሽነሪዎችና ቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ፣ የኢትዮጵያን የግብርና ሜካናይዜሽን፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለማስተዋወቅ እንዲሁም በኢትዮጵያና በጣሊያን የግሉ ዘርፍ መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር የማስተሳሰር ሥራዎችን ተከናውነዋል።
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራውና የምክር ቤቱን የቦርድ አባላት ያካተተው ልዑክ፣ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በኤግዚቢሽኑ ተሳትፏል።
በተሳትፎውም በኤምባሲው አስተባባሪነት በኢትዮጵያና በጣሊያን ኩባንያዎች መካከል የቢዝነስ ለቢዝነስ (B2B) ውይይቶች የተመቻቹ ሲሆን፣ በግብርና ማሽነሪ ግዢ፣ በአገር ውስጥ መገጣጠምና ማምረት፣ በጋራ ኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂና በዕውቀት ሽግግር እንዲሁም በሙያዊ ሥልጠና ላይ ያሉ የትብብር ዕድሎች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በተጨማሪም፣ ከኢትዮጵያ ገበያ የወጡ እና እንቅስቃሴያቸውን የቀነሱ የጣሊያን ኩባንያዎች ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ገበያ አንድመለሱ በኢንቨስትመንት ዕድሎች አንድሰማሩ የማሳመን ሥራ ተከናውኗል።
(በሮም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ)

