Feb 10, 2026 .
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አስተዳደር ( TVET Governance) ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አስተዳደር ( TVET Governance) ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ከጅ አይ ዜድ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ውይይት የተቋማቱ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በውይይቱም በፌደራልም ሆነ በክልል እንዲሁም በተቋም ደረጃ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና አስተዳደር ቅርጽ ምን መሆን አለበት? የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እነማን ናቸው? የግሉ ዘርፍ ሚና ምንድን ነው? የሚሉና ተያያዥ ጉዳዮች ተዳሰዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤትም የግሉን ዘርፍ የሚወክል ተቋም እንደመሆኑ በመንግሥትና በግሉ ሴክተር መካከል የተሻለ ግንኙነትና ውጤታማ ሥራ እንዲሠራ ሚናውን እንደሚወጣም በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

