በአዲሱ የስራ ዘመናችሁ ለላቀ ስኬት፣ ለጠንካራ አመራርና ለሀገራችን የበለጠ ልማትና ብልጽግና የሚያበረክት ውጤታማ አገልግሎት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ- የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 7ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመንግሥት መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲሁም ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ሆነው ተሰይመዋል።
እንዲሁም፤ የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እንዲሁም የተከበሩ አቶ ደስታ ሌዳሞን ደግሞ በምክትል አፈ ጉባኤነት ሰይሟል።

በመሆኑም፤ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ በመላው የንግዱ ማኅበረሰብ እንዲሁም በራሴ ስም እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ። በቀጣይም የምክር ቤቶቹ አመራሮች ከመንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ያለውን የጋራ ትብብር በማጠናከር፣ ለኢኮኖሚያዊ ልማት፣ ለኢንቨስትመንትና ንግድ ማስፋፊያ የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፍ በመፍጠር የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ እምነቴ ነው።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከሁለቱም ምክር ቤቶች ጋር በቅርበት በመሥራት የግሉ ዘርፍን ጥቅምና የንግዱን ማኅበረሰብ ድምፅ በማስተጋባት፣ ለአገራዊ ኢኮኖሚ ልማት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ የበለጠ ለማጠናከር ዝግጁ ነው።
በአዲሱ የስራ ዘመናችሁ ለላቀ ስኬት፣ ለጠንካራ አመራርና ለሀገራችን የበለጠ ልማትና ብልጽግና የሚያበረክት ውጤታማ አገልግሎት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።
የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

