Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራእና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

(የኢንዘማም፡ መስከረም 23/217 ዓ.ም)

በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል በተካሄደው ውይይት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እንዲሁም የክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተወካዮችና የግሉ ዘርፍ የቢዝነስ ተቋማት ተወካዮችና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተገኝተዋል፡፡

በCIPE አፍሪካ፣ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በጀርመኑ  Konrad-Adenauer-Stiftung (KAS) የተሰኘው ተቋም ድጋፍ በተዘጋጀው በዚህ ውይይት በተለይም በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ለኢትዮጵያ የቢዝነስ ዘርፍ ሊያጋጥሙ የሚችሉ እድሎችና ተግዳሮቶችን ለመለየትና ለመቅረፍ ያለመ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ውቤ መንግስቱ የኢትዮጵያ ቢዝነስ በአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና ስር የሚኖረውን ተጠቃሚነት ለማሳደግና ሊያጋጥሙ የሚችሉ እንቅፋቶችን በአግባቡ መረዳትና አወንታዊ እድሎችን ማስፋት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ምክር ቤቱ ሁልጊዜም ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ እና የግሉ ዘርፍ ተጠቃሚነት የሚያድግበትን እድል ለማስፋት እንደሚሰራ የተናገሩት አቶ ውቤ መሰል የአሰራር፣ ታሪፍ፣ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች፣ ተወዳዳሪነት እና መሰል ጉዳዮችን በጥናት በመለየት ተጠቃሚነትን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የመልቲላተራል ንግድ ግንኙነትና ድርድር ሲንየር ኤክስፐርት አቶ ገብረጻድቅ ጣሰው በበኩላቸው በንግድ ተወዳዳሪ ለመሆን የአፍሪካ ንግድ ቀጠና ስምምነት አተገባበርን በአግባቡ መረዳት እንደሚገባ ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የንግድ መግቢያ በር በመሆንና በካርጎ አገልግሎት ከሌላው የተሻለ ተነጻጻሪ እድል እንዳላት አንስተዋል፡፡

የምርትና አገልግሎት ዝርዝርን ለአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት ያሳወቀች ሲሆን ወደ ውጭ በሚላኩ ምርቶች እንዲሁም ያሉትን የገበያ እድሎች በተገቢው መልኩ ማወቅ እንደሚገባም ጠቁመዋል አቶ ገብረጻድቅ፡፡

የCIPE የኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አህመድ ሞሀመድ በበኩላቸው በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ሥምምነት ዙሪያ በኢትዮጵያ ያለውን የግሉ ዘርፍ ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ ጥናት መካሄዱንና ከዚህ በፊትም በትግራይ፣ በሲዳማና በድሬዳዋ ውይይቶች መካሄዳቸውን አንስተው አሁንም በጉዳዩ ዙሪያ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

የKonrad-Adenauer-Stiftung (KAS) የኢትዮጵያ ቢሮ ፕሮጀክት አስተዳደር ህይወት ታደሰ በበኩላቸው ድርጅቱ በአፍሪካ አጀንዳ 2063 ጉዳዮች እና በሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እየሰራ ሲሆን የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ውጤታማ እንዲሆን አስላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አንስተው ድጋፉ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ በስምምነቱ ትግበራ የሚያጋጥሙ ችግሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ቢዝነስ እድሎችና መፍትሄዎች ዙሪያ ጥናት የቀረበ ሲሆን በጥናቱ መሰረትም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia