Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 25, 2025 .

በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ምን አይነት ምርቶችን ይዘን ብንገባ ተወዳዳሪዎች ልንሆን እንችላለን ማለት ይገባል፡- ሐጅ አህመድ ሀሊፋ

በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዉስጥ ምን አይነት ምርቶችን ይዘን ብንገባ ዉጤታማ ተወዳዳሪዎች ልንሆን እንችላለን የሚለዉን ሁሉም የንግዱ ማህበረሰብ ሊያስብ እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የንግድና ዘርፍ ማሀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሐጅ አህመድ ሀሊፋ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች ዕድሎችና ስጋቶች ላይ ከክልሉ ለተዉጣጡ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምከር ቤት አመራሮች የተሰጠዉ ስልጠና ሲጠናቀቅ ባስተላለፉት መልዕክት ነዉ።
በስልጠናዉ ግንዛቤ ማግኘታቸዉንና መነቃቃትን እንደፈጠረላቸዉ የስልጠናዉ ተሳታፊዎች ገልፀዉ መሰል ስልጠናዎች እስከ ታች ድረስ መዉረድ አለባቸዉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ለስልጠናዉ ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ከሰጡ በኋላ ም/ቤታችን የአባላቱንና የመላዉ ንግድ ማህበረሰብ አቅምን ለመገንባት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ አቋቁሞ የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ ስለሆነ የስልጠና ፍላጎቶቻችሁን በማሳወቅ ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ ብለዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia