Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

በኢትዮጰያ የዘላቂ ስላም ግንባታ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ላይ የግሉን ዘርፍ ሚና ውይይት

በኢትዮጰያ የዘላቂ ስላም ግንባታ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ላይ የግሉን ዘርፍ ሚና በሚመለከት ውይይት የሚደረግበት የጋራ መድረክ ነገ በአዲስ አበባ  የዓድዋ መታሠቢያ ሊካሄድ  ነው፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በጋራ በሰጡት መግለጫ የምክክር መድረኩ “የግሉ ዘርፍ ሚና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ  ያለው ነው።

የመድረኩ የግሉ ዘርፍ በኢትዮጰያ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ጥረቶች ላይ ሚናውን  በሚያጠናክርበት ሁኔታ መግባባት ላይ የሚደረስበት ውይይት እንዲሁም የንግዱ ማኅበረሰብ በሀገረ መንግሥት ግንባታና ሰላም ላይ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ማበርከት እንዲችሉ ወጥ የሆነ የአፈጻፀም ሥርአት ለመዘርጋት ነው፡፡

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ አለመግባባቶች እና ግጭቶች ለልማት፣ ለሰላምና ለመሰረታዊ የዜጎች ደህንነት አስጊ እየሆነኑ መቀጠላቸው፤ ብሎም በረጅም ጊዜም ቢሆን ለአጠቃላይ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጦች እንዲሁም ለኢንቨስትመንት እና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ  መቀዛቀዝ ምክንያት ይሆናሉ።

በሌላው ጎኑ የግሉ ዘርፍ በጥራትም ሆነ በብዛት የተሻለ ምርት በዓለም ገበያ ላይ ከማቅረብ ባለፈ በሀገሪቱ ውጤታማና የተሳካ የቢዝነስ ምህዳር በዘላቂነት እንዲፈጠር ማስቻልና ዜጎች በቂ እና ጥራት ያለው የሀገር ውስጥ ምርት እንደፍላጎታቸው በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብላቸው ማድረግ እና ሀገሪቱ  የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል የመሆን ራዕይ እውን ለማድረግ ቁልፍ ጉዳይ ከመሆኑ አንጻር እነዚህንም ተግባራት ለማከናወን የሰላም መኖር ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

በመሆኑም፤ በሀገሪቱ ሰላምን ለማስፈንና ዜጎች የተረጋጋ ህይወት እንዲመሩ ከሌሎች ወገኖች የሚጠበቁ ኃላፊነቶች የመኖራቸውን ያህል ከግሉም ዘርፍ የሚጠበቁ በርካታ ኃላፊነቶች አሉ፡፡

በተጨማሪም፤ በሀገር ውስጥ ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም መገንባት የሚቻለው የውጭ ኢንቨስትመንትን በማበረታታት፣ የወጪ ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያ ያላቸውን ተደራሽነት በማስፋት እና የቱሪዝምን ፍሰት በማሳደግ እንዲሁም ዕውቀትና ቴክኖሎጂን በማሸጋገር ነው፡፡ ለዚህም የዜጎችን የስራ አጥነት በመቀነስ፣ የውጪ ምንዛሪ ግኝትን ማሳደግ፣ በወሳኝ ደረጃ ደግሞ ለግሉ ዘርፍ ዕድገት ማነቆ ሆነው የቆዩትን ህጎች እና አሰራሮች ማሻሻል ጭምር ነው፡፡

ለዚህም የውይይት መድረኩ መንግሥት ከሚያከናውናቸውና ዐበይት ስራዎች ባሻገር በሰላም ግንባታ ዙሪያ የግሉ ዘርፍ  ያለውን ሚና በማሳደግ  ረገድ  ትልቅ ሚና ይኖረዋል ፡፡

የመድረኩ ዓላማም የግሉ ዘርፍና የንግዱ ማኅበረሰብ በኢትዮጰያ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ላይ ገንቢ አስተዋፅዖ ማበርከት እንዲችል ተገቢ ሚና አንዲጫወት በማድረግና የጋራ ግንዛቤ  በመፍጠር ዘላቂና ወጥ የሆነ ሥርአት ለመዘርጋት ማስቻል ነው፡፡

በመድረኩ ከ500 በላይ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ነው።

መድረኩን  የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ም/ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴር እና ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተርፕራይዝ (CIPE) “የግሉ ዘርፍ ሚና በኢትዮጰያ ዘላቂ ሰላም ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ በቅንጅት ያዘጋጁት ነው፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia