Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 21, 2026 .

በኢትዮጵያ እና እና በተባበሩት አረብ ኤምሬት መካከል የቢዝነስ ግንኙነትን የሚያጠናክር የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

በኢትዮጵያ እና እና በተባበሩት አረብ ኤምሬት መካከል የቢዝነስ ግንኙነትን የሚያጠናክር የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሻርጃህ ንግድ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን የሚያስቃኝ እንዲሁም ከተባበሩት አረብ ኤምረትስ ከመጡ ባለሃብቶች ጋር የንግድ እና የኢንቨስትመንት እድሎችን መፍጠር የሚያስችል የቢዝነስ ፎረም አካሂዷል፡፡

በፎረሙ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ሃሰን መሃመድ ፡የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴርተወካይ በረከት መሰረት በአብዱላህ ሱልጣን አልዋላስ የሻርጃህ ንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር፡ አምባሳደር ደዋኖ ከድር ፡የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ መሃመድ እንዲሁም የቦርድ አባላት እና አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን በፍጥነት ማሳደግን ኢላማ አድርጋ እየሰራች መሆኑን በንግግራቸው ያነሱት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ሃሰን መሃመድ በአለም አቀፍ ደረጃ የቢዝነስ ግንኙነቶችን ከማሳደግ አንጻር የተባበሩት አረብ ኤምሬት ሃገራት በንግድ እና በሎጀስቲክስ በፋይናንስ በቴክኖሎጂ እና በኢንቨሰስትመንት አቅም ወሳኝ የቢዝነስ ግንኙነት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ተወካይ በረከት መሰረት በበኩላቸውም አሁን ላይ ኢትዮጵያ በለውጥ ላይ መሆኗን ጠቁመው ገበያን በማስፋት እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር እረገድ ትኩረት መሰጠቱን አና ከዚህም አንጻር ከሚደረጉት ስትራቴጂክ ግንኙነቶች ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ሃገራት ጋር ያለው ተጠቃሽ እንደሆነ ጠቁመዋል::

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመት ውስጥ ቡና ወደ እነዚህ ሃገራት በመላክ ቀዳሚ ሲሆን ሰሊጥ እና ስጋ በመቀጠል የሚቀመጡ መሆናቸውን አንሰውተዋል፡በተጨማሪም ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ወሳኝ የሆኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ማድረጓንም የገለጹ ሲሆን ይህ አካሄድ ኢንቨስትመንትን ወደሃገር ውስጥ ለመሳብ እና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በእለቱ የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ መሃመድን ወክለው ንግግር ያደረጉት የአዲስ ቻምበር ዋና ጸኃፊ አቶ ዘካርያስ አሰፋ በበኩላቸው ፎረሙ የንግዱ ማህበረሰብ እርስ በርስ ለመተዋወቅ እድል ሚፈጥር ብቻ ሳይሆን ወሳኝ የሆነ የኢኮኖሚ አጋርነት የሚመሰረትበት እንደሆነ አንስተው የኢትዮጵያ ያልተነካ እምቅ አቅም በግብርና፡ በማእድን ፡በአምራች ኢንደስትሪ፡በአይሲቲ እንዲሁም በቱሪዝም ያላትን እድል ክፍት አድርጋ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ሃገራትም ያላቸውን የሎጀስቲክስ፡የቴክኖሎጂ፡የካፒታልእና የኢንቨስትመንት አቅም በማጣመር ለጋራ ተጠቃሚነት ማዋል እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

በፎረሙ የሻርጃሕ ቻምበር ሊቀመንበር አብዱላህ ሱልጣን አልዋለህ የሻርጃህ ከተማ የኢንቨስትመንት አቅም እና ያሉ እድሎችን ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን ፡፡በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኩልም በኢትዮጵያ ያለው የኢንቨስትመንት እድልን አስመልክቶ ዘርዘር ያለ ማብራርያ ቀርቧል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል ያለውን የኢንቨስትመንት አሰራር እና ምቹ ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጎ በተካሄደው የፓናል ውይይትም ኢትዮጵያ በዋናነት እያከናወነች ባለችው የለውጥ ስራ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ እየሰራች መሆኑ ተጠቅሷል፡፡(የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት )

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia