Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 14, 2025 .

በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስት ያድርጉ በሚል መሪ ቃል ዛሬ አራተኛዉ አለም አቀፍ የማዕድን ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል በኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተከፍቷል።

በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስት ያድርጉ በሚል መሪ ቃል ዛሬ አራተኛዉ አለም አቀፍ የማዕድን ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል በኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተከፍቷል።

የአገራችን የግሉ ዘርፍ ድምፅና ተወካይ የሆነዉ የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የስራ አመራር አባላትም በኤክስፖዉ ላይ ተሳትፈዋል።

ከአባል ምክር ቤቶችም የኦሮሚያ የሲዳማ የደቡብ ኢትዮጵያ የሱማሌ የሐረሪ እንዲሁም የአዲስ አበባና የድሬደዋ ከተማ አስተዳር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንቶች ተካፍለዋል።

ኤክስፖዉን በንግግር የከፈቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ በተለያዩ የማዕድን ሀብት የታደለች አገር ብትሆንም እስከዛሬ ድረስ ከዘርፉ ያገኘችዉ ጥቅም በቂ እንዳልሆነ ጠቁመዉ አሁን ግን የአገር ዉስጥና የዉጭ የግሉ ዘርፍ አንቀሳቃሾችን በማሳተፍ ዘርፉን ለማልማት ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸዉን አስረድተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia