Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 11, 2026 .

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣  በመላው የንግዱ ማኅበረሰብ እንዲሁም በራሴ ስም  እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣  በመላው የንግዱ ማኅበረሰብ እንዲሁም በራሴ ስም  እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፤  ቀኑ ለሀገራችን ክብርና ነፃነት ደማቸውን እያፈሰሱ ላሉና ሕይወታቸውን የሰዉ ጀግኖቻችንን እያስታወስን ለሀገራዊ አንድነት የምንዘምርበት ብቻ ሳይሆን ለብሔራዊ መግባባት ፣ ለጋራ ዕድገት እና ልማት ያለንን ቁርጠኝነት የምናድስበት ጭምር መሆኑን እንገልፃለን ።

የግሉ ዘርፍ የሀገር ኢኮኖሚ ዋነኛ ሞተር እና  የዕድገት መሰረት በመሆኑ ለብሔራዊ አንድነትና ለጋራ ልማት ያለው አስተዋፅኦው ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃርም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ የሀገራችን ሉዓላዊነት፣ ነፃነት፣ ማንነትና የጋራ ዕድገትና እሴቶቻችን መገለጫ ነው የምንለውም ለዚህ ነው።

በተጨማሪም፤  ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን  ከጀግንነት ምልክትነቱ ባሻገር የኢትዮጵያ ምርቶችንና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥና በዓለም ገበያ የማስተዋወቅ የጋራ ኃላፊነታችንን በብቃት ለመወጣት እንዲቻለን ሞራል የሚያላብሰንም ነው።

“የኢትዮጵያን ይግዙ- በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ- ኢትዮጵያ  ታምርት- በኢትዮጵያ የተመረተ” የሚሉትን እሴቶች በጥራት፣ በፈጠራና በተወዳዳሪነት ማሳደግ የሀገራችንን ክብር ከማጠናከር ባሻገር፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግና የሀገር ውስጥ ሀብትን ለማሳደግ ያግዛሉ።

ከዚህም ባሻገር፤ ሰንደቅ ዓላማችን የሀገር ኩራትና የወደፊት ተስፋ ምልክት እንደመሆኑ፣ የግሉ ዘርፍ በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል ልማትና በዘላቂ ኢንቨስትመንት የሀገሪቱን የዓለም ገበያ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚያስችለን ስንቃችን ነው።

በመሆኑም ፤ በዚህ የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን፣ ሁላችንም ልዩነቶቻችንን በማክበር፣ የጋራ እሴቶቻችንን በማጠናከርና በትብብር በመሥራት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነትና ልማት ያለንን አስተዋፅኦ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድናጎለብት በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia