Feb 26, 2025 .
በዘላቂ ሰላም ግንባታ የግሉ ዘርፍ ሚናን በሚመለከት የውይይት መድረክ
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከ ሰላም ሚኒስቴር እና ከሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተርፕራይዝ (CIPE) ጋር በመተባበር በዘላቂ ሰላም ግንባታ የግሉ ዘርፍ ሚናን በሚመለከት የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ “የጋራ ትርክት ግንባታ እና ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ የግሉ ዘርፍ ሚና” የሚል ጹሁፍ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር በክቡር ሙዋዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የቀረበ ሲሆን “በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ግንባታ የግሉ ዘርፍ ሚና” የሚል ጹሁፍ ደግሞ ኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡

