Nov 21, 2025 .
ተቀመጠውን መስፈርት ያሟላ ምርትና አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች ማድረስ ለነገዋ ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ፋይዳው የላቀ ነው፡፡

ተቀመጠውን መስፈርት ያሟላ ምርትና አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች ማድረስ ለነገዋ ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ፋይዳው የላቀ መሆኑን በመገንዘብ በየደረጃው በከፍተኛ ትኩረት መስራት ይገባቸዋል፡፡
ከህዳር 11 እስከ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው በጥራት መንደር በተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ በምርቶቻቸውና አገልግሎቶቻቸው የጥራት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት ያገኙ ተቋማት ብቻ ታድመውበት ጥራታቸው የተረጋገጠ ምርትና አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡
ከአውደ ርዕዩ ጎን ለጎን ወደ ኢኮኖሚ ዘርፍ ለተቀላቀሉ አዳዲስ ተቋማትም ለሚያመርቱት ምርትና ለሚሰጡት አገልግሎቶች የተቀመጡ መስፈርቶችን ስለማሟላታቸው አስፈላጊው ፍተሸ ተደርጎ የጥራት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት እየተሰጠ ነው፡፡
እርስዎም የዘርፉ ተዋናይ ከሆኑ ምርትና አገልግሎትዎን በማዕከሉ አቅርበው በማስፈተሽ ተመራጭ የሚያደርግዎትን የጥራት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት በመውሰድ በገበያው ውስጥ የሚኖርዎትን ተፈላጊነትና ተወዳዳርነትን ይጨምሩ፡፡

