አኩሪ አተርን እሴት በመጭመር ወደ ገበያ የሚያቀርቡ ድርጅቶችና የማሽነሪ አቅራቢዎች የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄደ።
አኩሪ አተርን እሴት በመጭመር ወደ ገበያ የሚያቀርቡ ድርጅቶችና የማሽነሪ አቅራቢዎች የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄደ።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በGIZ- SRVC ፕሮጀክት ድጋፍ ያዘጋጀው ይህ ውይይት በተለይም በአኩሪ አተር ላይ እሴት በመጨመር ወደ ገበያ የሚያቀርቡ አካላት ማሽነሪዎችን ከሚያቀርቡ አካላት ጋር ነው ውይይት ያደረጉት።
የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ውቤ መንግሥቱ አኩሪ አተር ትኩረት የተሠጠው የግብርና ምርት ሲሆን በምክር ቤቱ በኩል በዘርፉ ለተሠማሩ አካላት ሥልጠናዎችን በመሥጠት ምርቱ ላይ እሴት ጨምሮ ወደ ገበያ በማቅረብና የሥራ እድል በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
ከማሽነሪ አቅራቢዎች ጋር በቅርበት በመሥራትም ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሣደግ ያሥፈልጋልም ነው ያሉት።
የውይይቱ ተሣታፊዎች በአዳማ ሳይንሥና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የዩኒቨርስቲው ቴክኖሎጅ ክፍልም ለአኩሪ አተር ማቀነባበርና እሴት መጨመር አስፈላጊ ማሽነሪዎችን መሥራት እንደሚቻል አስታውቋል።
የዩኒቨርስቲው የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት ኃላፊ ዶክተር ስንታየሁ ለገሰ በዩኒቨርስቲው በኩል በቀጣይነት የተሻሉ ቴክኖሎጅዎችን መሥራት እንደሚቻል ገልጸው በአኩሪ አተር ማቀነባበርና እሴት መጨመር በተመለከተ ዘመናዊ መሳሪያዎችን በተጠቃሚዎች ጥያቄና ፍላጎት መሰረት መስራትአ ንደሚል ተናግረዋል፡፡
በሜካኒካልና ቴክኒካል ሥራዎች በቂ ባለሙያዎች እና የማምረት አቅም አለን ያሉት ኃላፊው ለማምረትና ለመሥራት እንደሚቻል ገልጸዋል።
በሌላም በኩል የማሽነሪ አምራችና አቅራቢዎች በአኩሪ አተር ብቻ ሣይሆን እንደ ጤፍና በቆሎ ያሉ ምርቶችን የማቀነባበር ሥራዎችን የሚሠሩ መሣሪያዎችን አቅርበዋል።
በዝግጅቱ ላይ የአኩሪ አተር ምርትን ከእርሻ ማሣ ላይ ሣይባክን በቀላሉ መውቃት የሚችል ማሽን እየገጣጠሙና እያቀረቡ መሆናቸውን የተናገሩት የኤልያስ ጀነራል ኢንጅነሪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤልያስ በቀለ ምርትን ማምረት ብቻ ሣይሆን በተሥማሚ ሁኔታ ማከማቸት የሚችሉ በርካታ ምቹ መሣሪያዎች እንደሚያመርቱም ተናግረዋል።
የማሙሽ ጀነራል ማሽነሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ፈንታሁን በበኩላቸው የተለያዩ የግብርና ማሽነሪዎችን በመሥራትና በማቅረብ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
ሥለሆነም በማሽነሪ አቅራቢዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ተቀራርቦ መሥራት እንደሚገባና የእሴት መጨመር ሥራውም ተመጋጋቢ መሆን እንዳለበት በአጽንኦት ነው የተናገሩት።
በአኩሪ አተር ምርት ሂደት የማምረት እንዲሁም የእሴት መጨመርና ለገበያ ለማቅረብ እንደ ማሸግ ያሉ ተያያዥ ሥራዎችም ትኩረት ሊሠጣቸው እንደሚገባ ተነሥቷል።

