Oct 02, 2026 .
አዲሱ የአመራር ዘመናችሁ የክልሎቻችሁን እና ከተማ አስተዳደር ኢኮኖሚያዊ አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት የምትቀይሩበት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል-ሰብስብ አባፊራ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር በአፋር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሐረሪ ክልሎች፣ እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተካሄዱትን የመንግሥት ምስረታና የመክፈቻ ጉባኤዎች ተከትሎ፣ ክቡር አወል አርባ፣ ክቡር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ ክቡር አቶ ፍቅሬ አማን፣ ክቡር ኦርዲን በድሪ እና ክቡር አቶ አብዱላሂ አደን፣ የየክልሎቻችሁንና የከተማ አስተዳደሩን የአመራር ኃላፊነት በመረከባችሁ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ፕሬዚደንቱ በመልዕክታቸው አዲሱ የአመራር ዘመናችሁ የክልሎቻችሁን እና ከተማ አስተዳደር ኢኮኖሚያዊ አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት የምትቀይሩበት፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን የምታሳድጉበት እና የሥራ ዕድልን የምታሰፉበት የስኬት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።
የግሉን ዘርፍ እንደ ቁልፍ የኢኮኖሚ ልማት አጋር በማጠናከር ምቹ፣ ተወዳዳሪና ቀልጣፋ የንግድ አካባቢ መፍጠር በዚህ የአመራር ዘመን ወሳኝ ይሆናል። በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከየክልሎቹ እና ከተማ አስተዳደር የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ጋር በቅርበት በመሥራት የግሉን ዘርፍ አስተዋጽኦ ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጣለሁ ሲሉ አጠቃለዋል።

