Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 29, 2025 .

ኢትዮጵያ ምርጥ የቡና ዝርያዎቿን በቻይና የማከፋፈያ ማዕከል በዙሁዙው ከተማ ልትጠቀም ነው፡- ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ

▶️ ኢትዮጵያ ምርጥ የቡና ዝርያዎቿን በቻይና ሰፊ ገበያ ውስጥ ለማሰራጨት የሚያስችላትን ስትራቴጂካዊ የማከፋፈያ ማዕከል በዙሁዙው ከተማ ልትጠቀም መሆኑን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ዛሬ አስታወቁ።

▶️ ፕሬዚዳንቱ በቻይና-ኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የቡና ንግድ ማስተዋወቂያ ኮንፍረንስ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፤ የቡና ኢንዱስትሪው ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆኑን ተናግረዋል።

▶️ የቡናው ዘርፍ ለሀገሪቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ 25 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን፣

▶️ ከውጭ ምንዛሬ ግኝት ደግሞ 30 በመቶውን በመሸፈን የኢኮኖሚው ዋነኛ የጀርባ አጥንት እንደሆነም ጠቁመዋል።

▶️ በቻይና የሚቋቋመው ማዕከል የኢትዮጵያን ቡና ይበልጥ ተደራሽ ከማድረጉም ባለፈ፣ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ ሰንሰለት ውስጥ ያላትን ተጠቃሚነት ከፍ እንደሚያደርገው ፕሬዚዳንት ታየ ጠቁመዋል።

▶️ ቡና የኢትዮጵያ ማንነትና ሕይወት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ የቻይና ዜጎች ይህንን ምርጥ ጣዕም ያለውን የኢትዮጵያ ቡና የሕይወት ዘይቤያቸው አንድ አካል አድርገው እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia