Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 08, 2025 .

ከኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት የስራ ቡድን ሰብሳቢ አምባሳደር ርብቃ ፊሸር ላምብ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል፦ዶክተር ካሣሁን ጎፌ

 

ከኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት የስራ ቡድን ሰብሳቢ አምባሳደር ርብቃ ፊሸር ላምብ ጋር በባለብዙ ወገንና በሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ሂደት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል፦ ክቡር ዶክተር ካሣሁን ጎፌ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት የስራ ቡድን ሰብሳቢ አምባሳደር ርብቃ ፊሸር ላምብ ጋር በባለብዙ ወገንና በሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ሂደት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።

ከክቡር ሚኒስትሩ በነበራቸው  ውይይት በሁለቱም የድርድር ማዕቀፍ የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ መረጃ መለዋወጣቸውን የተናገሩት አምባሳደር ርብቃ በድርድር ሂደት ውስጥ የተስተዋሉ ማነቆዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሂደቱን ለማፋጠን ከስራ ቡድን አባል ሃገራት ጋር ለመወያየት ቃል ገብተዋል።

የኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድርን በመጪው መጋቢት ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት በመዶረግ ላይ ሲሆን በዚሁ አግባብ በከፍተኛ ትጋት ወሳኝ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንገኛለን ሲሉ ሚኒስትሩ ዶክተር ካሣሁን በውይይት ማጠቃለያ አንስተዋል። ን/ቀ/ት/ሚ

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia