ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ በድጋሚ ጠ/ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የተሰማኝን ከፍተኛ ደስታና ኩራት እገልፃለሁ-የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ

ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ በድጋሚ የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የተሰማኝን ከፍተኛ ደስታና ኩራት በራሴና በመላው የሀገራችን የንግድ ማህበረሰብ ስም እገልፃለሁ።
“ታሪክ የሚቀይር ኢትዮጵያዊ ራዕይን አንግቦ ሀገራችንን ከመበታተን የታደገ ፣የመደመር ዕሳቤ አባት፣ የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ፣ ሀገራችንን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሣሌት እያደረገ ያለ ባለ ምጥቁ አህምሮ የዘመናችን ምርጡ መሪ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ በድጋሚ የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ለኢትዮጵያ ልጆች ብቻ ሣይሆን ለአፍሪካም ታላቅ ዕድልና የመፂው ቀጣይ የብልፅግና ጉዞዓችን ዕውን መሆንን የሚያረጋግጥ ታላቅ ገድል በመሆኑ፤ በመላው ሀገራችንና በተለያዬ አህጉራት የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንኳን ደስ አላችው ማለት እወዳለሁ።”
መላው የንግዱ ማህበረሰብ ከምንግዜውም በላይ ከጀግናው መሪያችን ከክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ጎን በጠንካራ የስራና በመልካም ስነ ምግባር መንፈስ በመቆም ለዘላቂ ሰላም፣ አንድነት እና ሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ የበኩላችሁን አይተኬ ሚና እንድትወጡ አደራ እያልኩኝ፤ ከመንግስታችን ጋር በመሆን በቀጣይ የንግዱን ማህበረሰቡ ሁለንተናዊ መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናቅረን የምናስቀጥል መሆኑን አረጋግጣለሁ።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ክብሯን ጠብቃ ትኖራለኝ!
የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

