Feb 26, 2025 .
የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ በስካይላይት ሆቴል
የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ በስካይላይት ሆቴል
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ያዘጋጀውና በኢትዮጵያ ያለው የግብርና አሰራር ከአውሮፓ ህብረት ከደን ጭፍጨፋ-የፀዳ ደንብ (EUDR) ጋር ያለውን ተስማሚነት እንዲሁም፤ በኢትዮጵያ የአቮካዶ፤ ሽንኩርት፤ እና አኩሪ አተር ምርቶች የእሴት ሰንሰለቶች ውስጥ የሚገኙ የቢዝነስ አስቻይ ሁኔታዎች በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት ተካሄደ ፡፡
በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል የተካሄደው የምክክር መድረክ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በዘርፉ ላይ የመከሩበት ነው፡፡
በዚህ መድረክ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር እና የግብርና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ፤ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ም/ቤቱ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፤ የኩባንያዎች የስራ መሪዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላትና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

