Dec 01, 2025 .
የንግድ ዘርፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ወደ ተግባር እንዲገባ ተወሰነ።

የንግድ ዘርፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ወደ ተግባር እንዲገባ ተወሰነ።
የንግድ ዘርፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አብይ ኮሚቴ የንግድ ዘርፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታውን በጥልቀት ገምግሟል።
ኮሚቴው በግምገማው መሠረት የማስተካከያ ሀሳቦችን በመስጠት ፍኖተ ካርታው ወደ ተግባር እንዲገባ አቅጣጫ ሰጥቷል።

የንግድ ዘርፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አብይ ኮሚቴ ሪፎርሙን በበላይነት የመምራትና የመከታተል ኃላፊነት ያለው ሲሆን የሚኒስቴር መ/ቤታችን ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ዋና ዳይሬክተሮች እና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች የሚገኙበት ነው፡፡
የሪፎርም ሥራው በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር ሁሉም የሪፎርም ኮሚቴዎች የተጣለቸውን ተግባርና ኃላፊነት በትኩረትና በትጋት እንዲወጡ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ን/ቀ/ት/ሚ

