Dec 30, 2025 .
የአለም ንግድ ድርጅት ድርድር ብሄራዊ ኮሚቴ የባለብዙ ወገንና የሁለትዮሽ ድርድሮች ወቅታዊ ክንውኖችን ገምግመናል:- ዶክተር ካሳሁን ጎፌ

የአለም ንግድ ድርጅት ድርድር ብሄራዊ ኮሚቴ የባለብዙ ወገንና የሁለትዮሽ ድርድሮች ወቅታዊ ክንውኖችን ገምግመናል።
ሰሞኑን ስዊዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደው የአለም ንግድ ድርጀት ጠቅላላ ጉባኤ ያደረግነው ተሳትፎ ድርድሩን ወደፊት በመግፋት ያመጣውን አዎንታዊ ውጤት ለኮሚቴው አባላት ገልጫለሁ።
አስካሁን ከስምንት ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር መጨረሳችን አባልነትን ማሳካት የሚያስችል ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ከቀሪ ዘጠኝ አባላት ጋርም በፍጥነት ለመቋጨት በትጋት እየሰራን እንገኛለን።

ከዚህ በተጨማሪም ከ6ኛው የስራ ቡድን ስብሰባ በተነሱና በቴክኒክ ኮሚቴው በቀረቡ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አስተላልፈናል። የቴክኒክ ቡድኑ ለ7ኛው የስራ ቡድን ስብሰባ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን አጠናቆ ለሴክሬተሪያቱ እንዲያቀርብ አቅጣጫ አስቀምጠናል።
7ኛውን የስራ ቡድን ስብሰባ በመጪው የካቲት ወር ወስጥ ለማካሄድ የታቀደ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2026 የኢትዮጵያን አባልነት በስኬት ለመቋጨት በጠንካራ ተቋማዊ ቅንጅትና ትብብር መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
ዶክተር ካሳሁን ጎፌ
የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

