Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

May 25, 2026 .

የአትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር በየጊዜዉ እድገት እያሳየ ነው:- ሰብስብ አባፊራ

የአትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር በየጊዜዉ እድገት እያሳየ የመጣ ሲሆን ፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የግሉ ዘርፍ  የሁለትዮሽ ግንኙነት መጠናከርም ለዚህ ማሳያ ነው።

ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፤ ኢትዮጵያ የውጭ ንግድ መዳረሻ ስትሆን  በአሁኑ ወቅትም 169 ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርተው ይገኛሉ ፡፡

ዛሬ የተካሄደው የዱባይ- ኢትዮጵያ ቢዝነስ ፎረም  የጥንካሬው አንዱ ገፅታ ሲሆን፤  የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ዋና የወጭ ምርቶች መዳረሻ ሀገር እንዲሁም ዱባይ ለኢትዮጵያ ቢዝነሶች ምቹ የቢዝነስ አጋር መሆንዋን እና በርካታ የሀገሪቱ ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ በሥራ ላይ እንደሚገኙ መገለጫ ነው።

በቅርቡም  ኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡናዋን በዓለማቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የሚያስችላት 𝐒𝐩𝐞𝐜𝐢𝐚𝐥𝐭𝐲 𝐂𝐨𝐟𝐟𝐞𝐞 𝐚𝐭 𝐖𝐨𝐫𝐥𝐝 𝐨𝐟 𝐂𝐨𝐟𝐟𝐞𝐞 𝐃𝐮𝐛𝐚𝐢 𝟐𝟎𝟐𝟔 በዱባይ የዓለም ንግድ ማዕከል  ተካሂዷል።

በዚህ  ዓለም አቀፍ  የቡና ኤግዚቢሽን ላይም የኢትዮጵያ ቡና አምራቾች፣ ላኪዎች አልሚዎች እና እሴት ጭመራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች የተሳተፋበት ነበር።

በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግሩ መሰል ፎረሞች ተደርገዋል።

በዚህ አጋጣሚም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የአገር ውስጥ ምርትና አገልግሎትን ከማስተዋወቅ እንዲሁም የንግድና ኢንቨስት አማራጮችን ከማሳየት አንፃር መሰል ስራዎችን ከአቻ ምክር ቤቶች ጋር በመተባበር  የመከወን ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥልበት ይሆናል።

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት
❇️❇️❇️❇️❇️
Trade and investment relations between Ethiopia and the United Arab Emirates have shown  growth over time, and the strengthening bilateral engagement between the private sectors of the two countries is a clear indication of this progress.

For the UAE, Ethiopia has become an important foreign trade destination, while currently 169 UAE companies are engaged in various investment sectors in Ethiopia.

The Dubai–Ethiopia Business Forum held today is one reflection of this strong partnership. The forum highlighted that the UAE is one of the main destinations for Ethiopia’s export products, while Dubai serves as a favorable business hub and partner for Ethiopian businesses. It was also emphasized that many UAE companies are actively operating in Ethiopia.

Recently, Ethiopia also participated in the 𝐒𝐩𝐞𝐜𝐢𝐚𝐥𝐭𝐲 𝐂𝐨𝐟𝐟𝐞𝐞 𝐚𝐭 𝐖𝐨𝐫𝐥𝐝 𝐨𝐟 𝐂𝐨𝐟𝐟𝐞𝐞 𝐃𝐮𝐛𝐚𝐢 𝟐𝟎𝟐𝟔 exhibition held at the Dubai World Trade Centre, which provided an international platform to promote Ethiopian specialty coffee.

Ethiopian coffee producers, exporters, growers and value-addition investors participated in the global exhibition.

In addition, similar forums have been organized at different times to further elevate trade and investment ties between the two countries.

In this regard, the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) will continue strengthening its collaboration with counterpart chambers to promote Ethiopian products and services, while also showcasing trade and investment opportunities in Ethiopia.

Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia