Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Apr 19, 2025 .

የአቶ ሰለሞን አፈወርቅ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ በዮሴፍ ዘላቂ ማረፊያ ተፈፅሟል።

የቀድሞ ኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት (ቻምበርስ) ፕሬዚዳንት የነበሩት የአቶ ሰለሞን አፈወርቅ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ በዮሴፍ ዘላቂ ማረፊያ ተፈፅሟል።

በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአቶ ሰለሞን ቤተሰቦች እና ጓደኞቻቸው ተገኝተዋል።

በ1950 ዓ.ም በአሁኑ በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የተወለዱት አቶ ሰለሞን አፈወርቅ በሶዶ ሊጋባ በየነ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

በንግድ ሥራ ኮሌጅ በሒሳብ መዝገብ አያያዝ ዲፕሎማ እንዲሁም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በሁለኛ ድግሪ ተመርቀዋል።

በቀድሞ የሥጋ ሀብት ልማት ገበያ ድርጅት በደቡብ ቅርንጫፍ ለ6 ዓመታት ካገለገሉ በኋላ ፊታቸውን ወደ ንግድ በማዞር በጤና በትምህርት በእርሻ እና በሪል ስቴትስ ዘርፍ በመሰማራት ለሀገራች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለማበርከታቸው በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት የተነበበው የሕይወት ታሪካቸው ያመላክታል።

አቶ ሰለሞን በሕይወት ዘመናቸው የሐዋሳ ከተማ ንግድ ምክር ቤት እንዲቋቋም እና ተከፍቶ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረጋቸውም በላይ የደቡብ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት እንዲሁም የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክርቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ማገልገላቸው ተገልጿል።

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የፐብሊክ ተሳትፎ የኮሚቴ አባል በመሆንም የንግዱን ማኅበረሰብ በመምራት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በካናዳ በቢዝነስ ፈረሞች ሀገራቸው የማስተዋወቅ ሥራ ሠርተዋል።

የሁለቱ ሴቶች እና የሁለት ወንዶች አባት የነበሩት አቶ ሰለሞን አፈቀወርቅ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዘመዶቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።(EBC)

 

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia