Dec 14, 2025 .
የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአባላት መሠረቱን ለማስፋትና ለሁሉም ተደራሽ ለመሆን እያደረገው ያለው ጉዞ የሚበረታታ ነዉ:- ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ካካሄደው ተቋማዊ ለውጥ በኋላ የነበሩበትን የውስጥ እና የዉጭ ጫናዎች እየታገለ፤ የአባላት መሠረቱን ለማስፋትና ለሁሉም ተደራሽ ለመሆን እያደረገው ያለው ጉዞ የሚበረታታ መሆኑን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ገለፁ ።


የንግድ ምክር ቤቶች መሰረታቸው አባላት መሆኑ ይታወቃል ያሉት ፕሬዚዳንቱ የአዲስ አበባ የንግድ ማህበረሰቡም ጥላ ከለላውና ጠበቃው ለሆነው የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክርቤት የሚጠበቅበትን የአባልነት መዋጮ ወቅቱን ጠብቆ በመክፈል ማጠናከር እንደሚጠበቅበትና ሌሎች አባል ምክር ቤቶችም በተመሳሳይ መልኩ የአባል መሰረታቸዉን እንዲያሰፋ መልዕክት አስተላልፈዋል::

