Nov 23, 2025 .
የኢትዮጵያና የቱርክዬ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል የጠረጴዛ ዙርያ ዉይይት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያና የቱርክዬ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል የጠረጴዛ ዙርያ ዉይይት ከካሂደዋል።
በጠረጴዛ ዙርያ የምክክር መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ የሆነዉ አገር አቀፉ የንግና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከሐምሌ 2016 ጀምሮ እራሱን በአዲስ መልክ በማደራጀት የተቋቋመለትና ዓላማ ለማሳካት ከምንጊዜዉም በተሻለ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል።
ኢትዮጵያና ቱርክ የቆየ ጠንካራ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዳላቸዉ ያነሱት ዋና ፀሐፊዉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ ያደረገዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ለዉጭ ባለሀብቶች ተዘግተዉ የቆዩ የኢንቨስትመንት መስኮች መከፈታቸዉ ለቱርክዬ ባለሀብቶችም መልካም አጋጣሚ መሆኑን በማስረዳት በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል።
በዉይይት መድረኩ ከ25 በላይ በሚሆኑት የኢትዮጵያና የቱርክዬ ባለሀብቶች መካከል የአቻ ለአቻ የቢዝነስ ምክክሮችም ተካሂደዋል።




