May 14, 2025 .
የኢትዮጵያ- ቻይና (ሺጂያንግ) የቢዝነስ ትብብር ጉባኤ (Ethiopia-China Business cooperation and exchange conference ) በአዲስ አበባ ተካሄደ



የኢትዮጵያ- ቻይና (ሺጂያንግ) የቢዝነስ ትብብር ጉባኤ (Ethio-China Business cooperation and exchange conference ) በአዲስ አበባ ተካሄደ።
በዚህ ጉባኤ የውጭ ጉዳይ ሚኒሥትር ደኤታ አምባሣደር ሀደራ አበራ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሣደር ቼን ሀይ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ፣ የኢንዱሥትሪ ሚኒሥትር ደኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የቻይና (ሺንጂያንግ) እና የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ተወካዮች ተገኝተዋል።
የሁለቱ ሀገራት ኩባንያዎችም የቢዝነሥ ለቢዝነሥ ውይይት እና የመግባቢያ ሥምምነት እንደሚፈረም ይጠበቃል።




