Nov 06, 2025 .
የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳየው ትልቅ ተቋማዊ ለውጥና እድገት ለሌሎች ትልቅ ተሞክሮ እና ብርታት የሚሰጥ ነው፡- አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳየው ትልቅ ተቋማዊ ለውጥና እድገት ለሌሎች ትልቅ ተሞክሮ እና ብርታት የሚሰጥ ከመሆኑ አንጻር በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚገባው መሆኑን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ገለጹ::
የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የምስረታውን ግማሽ አመት አጠቃላይ ስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና ፋይናሻል ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም ወደፊት ስለሚከናወኑ ተግባራት ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር መስሪያ ቤት ከመጡ ባለሞያዎች ጋር ውይይት ማካሄዳቸው ተጠቅሷል::
በውይይቱም በጣም ውጤታማ ግማሽ አመት እንደነበረና ለወደፊትም ከዚህ በላይ ውጤት ለማምጣት አጠናክረን እንቀጥላለን ሲል የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የጠቀሰ ሲሆን በቅርቡም ማህበራችን የራሱ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ይኖረዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢርም ይህንን ውጤታማነት ጠቅሰው ነው ተግባራችሁ ለሁሉም ምሳሌ ይሆናል ያሉት።

