Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የለውጥ ሥራዎችን በተጠናከረ መልኩ መተግበር ተጀምሯል፡- ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ -የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ

የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት፤ ዓለም አቀፍ መሰል ምክር ቤቶች በደረሱበት የአገልግሎት አሰጣጥ እና የግንኙነት ደረጃ ልክ ውጤታማ እንዲሆን፤ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለውን የድልድይነት ሚና በአግባቡ እንዲወጣ እንዲሁም በምክር ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ የተሰጡትን ተልዕኮዋች በሚፈለገው ልክ ተግባራዊ ለማድረግ የለውጥ ሥራዎችን በተጠናከረ መልኩ መተግበር እንደተጀመረ አዲሱ የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሣ ለሚ ተናገሩ።

ቀደም ሲል የጅማ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩትና በቅርቡ ምክር ቤቱን የተቀላቀሉት ዶክተር ቀነኒሣ ለሚ ከምክር ቤቱ ሠራተኞች ጋር ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን፤ ምክር ቤቱን በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል እንደ ድልድይ በመሆን በአጠቃላይ የአገሪቱ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ስረዓት ውስጥ ወሰኝ ተጽእኖ ፈጣሪ ለማድረግ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤትን በተለይም በስትራቴጂ እንዲመራ የማድረግ፣ አገልግሎት አሰጣጡ የሚፈልገው መዋቅራዊ አሰራር በመዘረጋት፣ ከአባላት ጋር ያሉትን ግንኙነቶች በማጠናከር እንዲሁም የሠራተኛውን አቅም በማሣደግና የተሻሻሉ አሠራሮችን በመተግበር እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ የሚሠጣቸውን አገልግሎቶች በማዘመን፣ ከመንግሥት ተቋማት እንዲሁም ከዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በትብብር እንደሚሠራ ነው ዶክተር ቀነኒሣ የጠቀሡት።

21 አባል ምክር ቤቶችና ማኀበራት ያሉት ምክር ቤቱ የአባላቱን አቅም የማሳደግ፤ ኃላፊነቶቻቸውን እና ግዴታዎቻቸውን እንዲወጡ የማበረታታት፤ በሁሉም አሰራሮች ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የማብቃት እና የመደገፍ ስራዎችም ቁልፍ ተግባራት ናቸው ብለዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia