May 06, 2025 .
የኢትዮጵያ -እስራኤል ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ

የኢትዮጵያ -እስራኤል ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ።
የረጅም ዘመን ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ኢትዮጵያ እና እሥራኤል ያላቸውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሣደግ የሚያሥችል የሁለትዮሽ ቢዝነሥ ለቢዝነሥ ፎረም በአዲስ አበባ ሀያት ሬጀንሲ ሆቴል ነው የተካሄደው።
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒሥትር ጌዲዮን ሳአር በፎረሙ ላይ ተገኝተዋል።
በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ ኢንቨሥትመንት ሆልዲንግስ፣ ከኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ኢንቨሥትመንት ኮሚሽን እንዲሁም ከኢንዱሥትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና የሌሎች ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል።
የእሥራኤል አምራቾች ማኀበርና የኤክሥፖርት እና ዓለም አቀፍ ትብብር ኢንሥቲትዩትን ጨምሮ ከሁለቱ ሀገራት የተውጣጡ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሠማሩ ተቋማት እና ኩባንያዎች በፎረሙ ላይ ተገኝተዋል።
ፎረሙም ሁለቱ ሀገራት ያሏቸውን የቢዝነስ እድሎች ለማየትና ኩባንያዎችም በጋራ መሥራት የሚችሉ





