Nov 13, 2025 .
የኢትዮጵያ እና ስዊድን የቢዝነስ ለቢዝነስ ውይይት (B2B) በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሄደ።

የኢትዮጵያ እና ስዊድን የቢዝነስ ለቢዝነስ ውይይት ( B2B) በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሄደ።
በውይይቱም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ፣ የስዊድን የምሥራቅ አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጆአኪም ዳቪድሠን እንዲሁም የኢትዮጵያ እና ስዊድን ኩባንያዎች ተገኝተዋል።
ውይይቱ የሁለቱ ሀገራት ቢዝነስ ልውውጥ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ እንዲል አበርክቶ ይኖረዋል ተብሏል።

የስዊድን ኩባንያዎች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ፣ በታዳሽ ሀይል፣ በመልሶ መጠቀምና በሌሎችም የማምረቻ መሥኮች የተሻለ አቅም ያላቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር በትብብር መሥራት እንደሚፈልጉ ጆአኪም ዳቪድሠን ገልጸዋል።
የስዊድን የምሥራቅ አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት እንደ ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በኢትዮጵያም የመሥራት ፍላጎት እንዳለው ተጠቁሟል።


