Dec 11, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከህንድ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከህንድ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ ።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አይናለም ዓባይነህና የህንድ ንግድና ኢንዱስሪ ምክር ቤት ጆይንት ዳይሬክተር አሸሽ ካትሪ ናቸው።
የኢትዮ – ህንድ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አዳራሽ እየካሄደ ነው፡፡ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የህንድ ኩባኒያዎችን ያካተተ የቢዝነስ ልዑካን በፎረሙ እየተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያ ዉስጥ ስላሉ የቢዝነስና የኢንቨርስትመንት አማራጮች ገለጻ ተደርጎላቸዋል ፡፡
በፎረሙ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ ፣ የኢትዮጰያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዝናቡ ይርጋ ፣ በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኤዝያና የመካከላቸው ምስራቅ ዳይሬክተር ጄኔራል አምሃ ሀይለ ጊዮርጊስ እንዲሁም የህንድ ንግድና ኢንዱስትሪ ም/ቤት ጆይንት ዳይሬክተር አሽሽ ካትሪ በተገኙበት ፎረም እየተካሔደ ነው ::

