Feb 11, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ሄለን ረታ ከ4ኛዉ የህገ ወጥ ንግድ ኮንፈረንስ የቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በኮንፈረንሱ ቅድመ ዝግጅት ላይ ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ሄለን ረታ ከ4ኛዉ የህገ ወጥ ንግድ ኮንፈረንስ የቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በኮንፈረንሱ ቅድመ ዝግጅት ላይ ተወያይተዋል።

የኮንፈረንሱ ቴክኒክ ኮሚቴ ህገ ወጥ ንግድን በመከላከልና በመቆጣጠር ጉልህ ሚና ካላቸዉ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር፣ ከገቢዎች ሚንስቴር፣ጉሙሩክ ኮሚሽን፣ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስቴር፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና ከኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የተዉጣጡ አባላትን ያካተተ ሲሆን በኮንፈረንሱ ላይ ሊሳተፉ የሚገባቸዉ ቁልፍ ተቋማትን የመለየትና ህገ ወጥ ንግድ በስፋት የሚስተዋልባቸዉን ኮሪደሮችን መለየት በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተዋል::
4ኛዉ ህገ ወጥ ንግድን በመከላከል ላይ የሚያተኩረዉ አገር አቀፍ ኮንፈረንስ የካቲት 17 ቀን በአዲስ አበባ ይካሄዳል።