የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት Africa in Motion ከተባለ ድርጅት ጋር አብሮ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይቷል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት Africa in Motion ከተባለ ድርጅት ጋር አብሮ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይቷል።
የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የንግዱን ማህበረሰብ አቅም ከመገንባት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየሰራ መሆኑን የም/ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳጨለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) በማስረዳትበተለይም በሴቶች ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች የሚንቀሳቀሱ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ከማብቃት አንፃር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለስራ ዕድል ፈጠራና ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት እያበረከቱ ካሉት አስተዋፅኦ አንፃር ተገቢዉ ትኩረት እንዳልተሰጣቸዉ ያነሱት ዶ/ር ቀነኒሳ የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እነዚህ ተቋማት በአገሪቱ እንደ አዲስ በተጀመረዉ የካፒታል ገበያ ዉስጥ ተገቢዉን ድርሻ እንዲኖራቸዉ ለማስቻል እየሰራ ነዉ ብለዋል።

ስለሆነም Africa in Motion ሴት ስራ ፈጣሪዎችን በሚያበረታታበት Equal Tarade Alliance ቀተሰኘዉ ፕሮግራሙ ከም/ቤቱ ዓላማ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ አብሮ ለመስራት ምቹ ሁኔታ መኖሩን አብራርተዋል።
የAfrica in Motion ዳይሬክተር ሚስተር ማክስ ኮፊ በበኩላቸዉ የድርጅታቸዉ ተልዕኮ ከኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ተልዕኮጨጋር እጅጉን የሚጣጣምና በዋና ዋና የም/ቤቱ ዓላማዎችና ተልዕኮዎች በአቅም ግንባታ ስልጠና በፖሊሲና አድቮኬሲ ላይ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ አሳዉቀዋል።

